ፋሲል ግቢ

myESAi Forum Index » General Discussion

Post new topic  Reply to topic

WaliaIbex
Lij

Send private message

View user's profile
Thu Jun 30, 2011 12:02 am   
ፋሲል ግቢ
_______________________________________________________________________________
ፋሲል ግቢ ወይንም በሌላ ስሙ ማቀባበያ ወይንም ነገሥታት ግቢ በጎንደር የሚገኝ ከአጼ ፋሲለደስ እስከ እቴጌ ምንትዋብ የተለያዩ ነገስታት በአንድ ግቢ (ቅጥር) ውስጥ ያሰሩትን የግንቦች ስብስብ የሚያገልጽ የቃላት ሐረግ ነው። ይህ ግቢ በጥንቱ ዘመን የአስተዳደር ስርዓት ተቀርጾለት በጥንቃቄ የሚመራ ነበር። ስርዓቱም ስርዓተ መንግስት በመባል ሲታወቅ በመጽሃፍ መልኩ በግዕዝና በድሮው አማርኛ የተመዘገበ ነበር።
በአሁኑ ወቅት ግቢው የፋሲለደስ ግምብን፣ ትንሹ የፋሲል ግምብን፣ የታላቁ እያሱ ግምብን፣ የዳዊት ፫ ዙፋን ቤትን፣ ምንትዋብ ግምብን፣ የየምንትዋብ ቱርክ መዋኛ፣ ፈረሶች ቤት፣ የፈረሰኞች አለቃ ቤትን፣ አንበሶች ቤት፣ የበካፋ ግምብ፣ በካፋ ሰገነት፣ የቀዳማዊ ዮሐንስ ጽሕፈት ቤትን፣ ዮሐንስ ቤተ መጻሕፍትን፣ ግምጃ ቤት ማርያምን፣ አጣጣሚ ሚካኤልን፣ አዋጅ መንገሪያን፣ ክረምት ቤትን፣ ቋል ቤት(የሰርግ ቤት)ን ያጠቃልላል። ከፋሲል ግቢ ወጣ ብሎ በስተሰሜን (እታች ካለው ምስል በስተቀኝ) ራስ ግምብ ይገኛል። የፋሲል ግቢ በሮችም የራሳቸው ስም ያላቸውና ለልተወሰነ ግልጋሎት የተሰሩ ነበር፣ በሮቹም ልዕልት እንኳየ (የምንትዋብ እናት_ በር፣ ግምጃ ማርያም በር፣ ጃን ተከል በር፣ ወምበር በር (የዳኞች በር) ፣ ተዝካር በር፣ አዛዥ ጥቁር በር፣ አደናግር በር፣ ቋል በር፣ እምቢልታ በር፣ ራስ በር፣ ዋናው በር፣ እርግብ በር ነበሩ። ከታች ካለው ስዕል ላይ በማውስወ ሊያገኟቸው ይችላሉ።
የሚከተለው ካርታ ላይ ማውስወን ቢያንሳፍፉ፣ እያንዳንዱ የግቢው ህንጻና በሮች ስም ወጥቶ ይታየወታል፡፡ ሲጫኑም ወደዚያ ክፍል ማብራሪያ ይወስደወታል።[1]
-------------------------------------------------------------------------------------------------------------------

myESAi Image

:arrow: ጊዜ ሲያገኙ ወደ ውክፔዲያ ጎራ ይበሉ፣ መልካም ምሽት :!: :!: :arrow: http://am.wikipedia.org

myESAi Forum Index » General Discussion » ፋሲል ግቢ » Reply to topic

. . .
. Most users ever online was 252 on Mon May 14, 2012 9:07 am.